Elegant New Blog Post Instagram Post

በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የክፍያ ካርድ (International Card) ለማውጣት ተቻለ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ አጠቃቀምን በተመለከተ አዳዲስ ማሻሻያዎችን ይፋ አድርጓል። ከእንግዲህ የውጭ ምንዛሬ አካውንት ያላቸው ደንበኞች የቪዛ እና የበረራ ትኬት ማቅረብ ሳይጠበቅባቸው ለዓለም አቀፍ የበይነ መረብ (ኦንላይን) ግብይቶች የሚውል የክፍያ ካርድ ማግኘት ይችላሉ።

በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የክፍያ ካርድ ለማውጣት ተቻለ!

ዋና ዋና ለውጦች፦

  • የቪዛ እና ትኬት ግዴታ ቀርቷል፦ ለኦንላይን ግብይት እና ሰብስክሪፕሽን የሚውል ዓለም አቀፍ ካርድ ለማውጣት ከእንግዲህ የጉዞ ሰነድ አይጠየቅም።
  • የ100 ዶላር ዝቅተኛ ተቀማጭ ቀርቷል፦ የውጭ ምንዛሬ አካውንት ለመክፈት የነበረው የ100 ዶላር የግዴታ ተቀማጭ ተነስቶ፣ መጠኑን ባንኮች ራሳቸው እንዲወስኑ ተፈቅዷል።
  • ለሕክምና እና ትምህርት፦ ወደ ውጭ ለሚጓዙ ሰዎች ያለ ቪዛ እና ትኬት እስከ 20,000 ዶላር ማግኘት ተፈቅዷል።
  • ገንዘብ ወደ ውጭ መላክ፦ ለትዳር አጋር እና ልጆች የትምህርት እና ሕክምና ክፍያ፣ እንዲሁም ለዘመዶች እገዛ እስከ 3,000 ዶላር መላክ ይቻላል።
  • ያለ ገደብ ምንዛሬ፦ ማንኛውም ሰው ይዞት የሚገባውን የውጭ ምንዛሬ መጠን ሳይገደብ በባንክ መመንዘር ወይም ማስቀመጥ ይችላል።

Read English

Digital Construct

Spread the love

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *